ምን አዲስ ነገር አለ?

የአውሮፓ ማዕከል አዲስ ድረ ገጽ ለቀቀ

በማኅበረ ቅዱሳን ከሀገር ውጪ ከሚገኙት ማእከላት አንዱ የሆነው የአውሮፓ ማእከል ትምህርተ ሃይማኖትን የሚያስተላልፍበት እና አገልግሎቶቹን የሚያስተዋውቅበት አዲስ ድረ-ገጽ ለቀቀ።

ዝርዝር ንባብ...

አዳዲስ ዜናዎች

ሀገረ ስብከቱ አብይ ጉባዔ አደረገ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ፤ ደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በሮም ኢጣሊያ የሀገረ ስብከቱ አብይ ጉባዔ ተደረገ።

ዝርዝር ንባብ...

RSS Feeds

feed-image Feed Entries
የቅድስት ማርያም ዘር ነኝ አትም ኢሜይል

በዲን. ብርሃኑ ታደሰ

ግንቦት 1፣ 2004 ዓ.ም.

አባታችን አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ለሚያመልኩ ሁሉ ታላቅ የእምነት አባት ነው። በእርግጥም አምላኩን ፍጥረትን በመመርመር ማግኘቱ፣ አምላኩን ብሎ ቤተሰቡን ተለይቶ መውጣቱ፣ ልጁን ለመሰዋት ፍጹም ፈቃዱን ማሳየቱ ሁሉ ለእምነት አባትነቱ ማሳያዎች ናቸው። ከሁሉ የሚልቀው ከእርሱ አስቀድሞ ከሙታን መካከል የተነሱ ሳይኖሩ፣ ዘርህ በይስሐቅ ይጠራልሃል ከተባለ በኋላ ልጅህን ሰዋልኝ ሲባል፣ እነዚህን ሁለት የሚጣሉ የሚመስሉ ሐሳቦችን በእምነቱ አስታርቆ ማለት ቢሞት እንኳን ያስነሳዋል ብሎ አምኖ ልጁን ሊሰዋ ወደ ተራራ መውጣቱ ነው።(ዕብ11፥19) የሰው ሕሊና ጊዜ ሲያገኝ አንድን ነገር ደጋግሞ ማሰቡ አይቀርም፤ አብርሃም ግን የሦስት ቀን መንገድ ሲሄድ ይህ እምነቱ ንውጽውጽታ አልነበረውም - እፁብ ነው።Lideta_Le_Mariam_1

እኛ ክርስቲያኖች - የእግዚአብሔር ወልድን ሰው መሆን፣ ለኛ ብሎ መከራ መቀበል፣ በኋላም የቤዛነቱን ሥራ ሲፈጽም በአባቱ ክብር መቀመጡን ስለምናምንና ስለተጠመቅን የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል። ይህ ልጅነት በፊት እንደነበረው ከሥጋ የመጣ አይደለም፤ መጽሐፍ - “ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደ ግን መንፈስ ነው።” እንዲል፤ ልጅነታችን በጸጋ ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ ነው። (ዮሐ3) ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ይህንን ሲያጸናው የተወለድነው ከሚጠፋ ዘር አይደለም ይለናል። (1ጴጥ1፥22)

ዝርዝር ንባብ...
 
ልዩ የፓልቶክ ውይይት አትም ኢሜይል
gedamatdiscussionad
 
ትንሣኤ አትም ኢሜይል
የተፃፈዉ በ ዲን. ብሩክ አሸናፊ   
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ሲነገር አብሮ የሚነሣው በዕለተ ዓርብ ስለኛ ብሎ የተቀበለው ሞቱ ነው። አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን በፈጸሙት በደል ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ሳለ በበደላቸው ንስሐ ገብተው አምላካችንን በመለመናቸው፥ እርሱም የሰው ፍቅር አገብሮት በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ሞቶ ሶስት መዓልት እና ሶስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ። ነገር ግን ተነሣ የሚለውን ለማመን ሞተ የሚለውን ማመን ስለሚቀድም፥ ጌታችን በዕለተ አርብ መሞቱን የቅዱሳት መጻህፍትን ምስክርነት በማስቀደም እንጀምራለን።
ዝርዝር ንባብ...
 
ሆሣዕና አትም ኢሜይል

በኤርምያስ ልዑለቃል

መጋቢት 29 2004 ዓ.ም.

ሆሣዕና ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጉሙም አሁን አድን ማለት ነው። በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የታላቁ ዓቢይ ጾም ስምንተኛ እሑድ የሆሣዕና በዓል በድምቀት የሚከበርበት ዕለት ነው። በዚህ ዕለት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ትህትና በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ያደረገውን ጉዞ የሚዘክር ቃለ እግዚአብሔር በስፋት ይደርሳል። በአራቱም ወንጌላውያን በቅዱስ ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና፣ ዮሐንስ ይህንኑ የፍጹም ትህትና እና የፍቅር ጉዞ አስመልክቶ የተጻፉ የወንጌል ክፍሎች  (ማቴ 21፥1-17 ፣ ማር 11፥1-10 ፣  ሉቃ 19፥28-44 ፣ ዮሐ 12፥9-19) በቅድስተ ቤተ ክርስቲያን ዑደት እየተደረገ በአራቱም አቅጣጫዎች ይነበባሉ።

Hosaena_icon_1


”አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል” ዘካ 9፥9

ዝርዝር ንባብ...
 
ኒቆዲሞስ አትም ኢሜይል

፩ መግቢያ

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የእምነቱ ተከታዮች ሁሉ እንዲጾሟቸው መጀመሪያቸውና መጨረሻቸው ተቀምሮ ጊዜና ወቅት ተወስኖላቸው የተደነገጉ ሰባት የዐዋጅ አጽዋማት አሉ።

እነዚህም አጽዋማት በሐዋርያት ሲጾሙ የቆዩና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና መጻሕፍት የአጿጿም ሥርዓታቸውን የሠሩላቸው ናቸው። ከእነዚህም ሰባት አጽዋማት አንዱና ዋናዉ ዐቢይ ጾም ነው። ይህ ጾም ክብር ምሥጋና ይግባዉና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ፵ መዓልትና ፵ ሌሊት ከቆመ ሳያርፍ ከዘረጋ ሳያጥፍ በትኅርምት የጾመዉ ጾም በመሆኑ ዐቢይ ተብሏል። ማቴ ፬፥፩። እኛም አምላካችን የጾመዉን ጾም ለማስታወስ፥ በረከቱን ለማግኘት፥ እርሱን አርዓያ አድርገን የሥጋ ፈቃዳችንን ለነፍስ ፈቃዳችን ለማስገዛት እንጾመዋለን። በዚህ ጾም ከተድላና ከደስታ ወገን ማናቸውንም ማድረግ እንዳይገባና ሁሉም ጿሚ ከሥጋዊ ነገር መጠበቅና መጠንቀቅ እንደሚገባዉ ተጽፏል። ዐቢይ ጾም አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ድኅነተ ዓለም የተቀበለዉን መከራ በማሰብ የምናዝንበት፥ በቸርነቱ በሰጠን ኃይል መንፈሳዊ ከሰይጣንና ከፈቃደ ሥጋ ጋር የምንጋደልበት፥ እኛ በበደልን እርሱ ክሦ እንዳዳነን በማዘከር ደግሞ ወደ ኃጢአት ላለመመለስ ቃል የምንገባበት፥ አብነት ሊሆነን ከኖረልን ሕይወትና ከሠራልን ሕግ የምንማርበትና ለቅዱስ ቁርባን የምንዘጋጅበት እጅግ የከበረ ወቅት ነው። እነዚህ የጾም ዕለታት ለሌሎች ጊዜያት ስንቅ የምንይዝባቸውና ተኩላ ከሆነው ሰይጣን የምንጠነቀቅባቸዉ መሆናችዉም በዓመቱ ዉስጥ ከሚኖሩት ቀናት ሁሉ ልዩ ያደርጋቸዋል።

ዝርዝር ንባብ...
 
ደብረ ዘይት አትም ኢሜይል

ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:-ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሰረት ነገረ ምጽአቱን (የመምጣቱን ነገር) እንድናስታዉስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነዉ።debre Zeyt

ዝርዝር ንባብ...
 

አዳዲስ ዜናዎች

ሀገረ ስብከቱ አብይ ጉባዔ አደረገ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በደቡብ፤ ደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በሮም ኢጣሊያ የሀገረ ስብከቱ አብይ ጉባዔ ተደረገ።

ዝርዝር ንባብ...

የዕለቱ ጥቅስ

ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ። ገላ. ፮፡፲፬

ግጻዌ